አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
ነህምያ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ከእነርሱም የተነሣ በአንጻራቸው ተጠባባቂዎችን በሌሊትና በቀን አደረግን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ግን ወደ አምላካችን ጸለይን፤ ዛቻቸውንም ለመቋቋም ቀንና ሌሊት የሚጠብቁ ዘቦችን መደብን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፥ ጠላቶቻችን በእኛ ዘንድ እንደታወቀ፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው በሰሙ ጊዜ፥ እኛ ሁላችንም ወደ ቅጥሩ፥ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ግን ወደ አምላካችን ጸለይን፤ እነርሱንም ለመቋቋም ሌሊትና ቀን ቆመው የሚጠብቁ ዘበኞችን መደብን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አምላካችንም ጸለይን፥ ከእነርሱም የተነሣ በአንጻራቸው ተጠባባቂዎች በሌሊትና በቀን አደረግን። |
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
ጠላቶቻችንም፥ “ወደ መካከላቸው እስክንመጣና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጕል ድረስ አያውቁም፤ አያዩም” አሉ።