ነህምያ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አንጻር ያለውን ሠራ። በአጠገቡም የአሰብንብሔም ልጅ ሐጡስ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ፤ የአሰበንያ ልጅ ሐጡስ ደግሞ ከርሱ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም የሐሩማፍ ልጅ ዬዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የሐሻቤኔያ ልጅ ሐጡሽ አደሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሩማፍ ልጅ የዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት የሚገኘውን ክፍል ሠራ። ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሐሻበንያ ልጅ ሐቱሽ ሠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የኤርማፍ ልጅ ይዳያ በቤቱ አንጻር ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የአሰበንያ ልጅ ሐጡስ አደሰ። |
ከእነርሱም በኋላ ብንያምና አሴብ በቤታቸው አንጻር ያለውን ሠሩ። ከእነርሱም በኋላ የሐናንያ ልጅ የመዓስያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን ሠራ።
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”