በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖን ሹሞች እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፥ “እናንት ዛሬ ስለምን አዝናችኋል?”
ነህምያ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ሳትታመም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኀዘን ነው እንጂ ሌላ አይደለም” አለኝ። እጅግም ብዙ አድርጌ ፈራሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ንጉሡ፣ “ሳትታመም ፊትህ ለምን እንዲህ ዐዘነ? መቼም ይህ የልብ ሐዘን እንጂ ሌላ አይደለም” አለኝ። እኔም በጣም ፈርቼ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፦ “አልታመምክም ታዲያ ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኃዘን ነው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም” አለኝ። እኔም እጅግ በጣም ፈራሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም “አንዳች የልብ ሐዘን ቢደርስብህ ነው እንጂ ሳትታመም እንዴት ይህን ያኽል በፊትህ የሐዘን ምልክት ይታያል?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እጅግ በመፍራት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ “ሳትታመም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኅዘን ነው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም” አለኝ። እጅግም ብዙ አድርጌ ፈራሁ። |
በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖን ሹሞች እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፥ “እናንት ዛሬ ስለምን አዝናችኋል?”