ሀገሪቱም ሁላ በታላቅ ድምፅ አለቀሰች። ሕዝቡም ሁሉ በቄድሮን ወንዝ ተሻገሩ፤ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተሻገሩ።
ነህምያ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌሊትም በፈፋው በኩል ወጥቼ ቅጥሩን ተመለከትሁ፤ በሸለቆውም በር ገባሁ፤ እንዲሁም ተመለስሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ቅጥሩን እየተመለከትሁ ሌሊቱን ሸለቆውን ዐልፌ ወደ ላይ ወጣሁ፤ በመጨረሻም ተመልሼ በሸለቆው በር በኩል ገባሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊት በፈፋው በኩል ወጥቼ ቅጥሩን ተመለከትኩ፤ ተመልሼም በሸለቆው በር ገባሁ፥ ከዚያም ተመለስኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሌሊቱን ወደ ቄድሮን ወንዝ በመውረድ፥ ቅጽሮችን እየጐበኘሁ አልፌ ሄድኩ፤ በመጨረሻም በዚያው በመጣሁበት መንገድ ተመልሼ በሸለቆው ቅጽር በር በኩል ወደ ከተማይቱ ገባሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌሊትም በፈፋው በኩል ወጥቼ ቅጥሩን ተመለከትሁ፤ ዘወርም ብዬ በሸለቆው በር ገባሁ፤ እንዲሁም ተመለስሁ። |
ሀገሪቱም ሁላ በታላቅ ድምፅ አለቀሰች። ሕዝቡም ሁሉ በቄድሮን ወንዝ ተሻገሩ፤ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተሻገሩ።
ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር፥ ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።
ጠባቆች ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤ ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹሞቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች እስከዚያ ጊዜ ገና አልተናገርሁም ነበር።
ሐኖንና የዘናን ሰዎችም የሸለቆውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ፤ ደግሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደዚያ ገባ።