Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማእዘኑ በር፣ በሸለቆው በርና በቅጥሩ ማእዘን ማማዎች ሠርቶ መሸጋቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዖዝያ በማእዘን ቅጽር በር፥ በሸለቆ ቅጽር በርና በቅጽሩም መጠምዘዣ ላይ መቈጣጠሪያ ግንቦችን በመሥራት የኢየሩሳሌምን ምሽጎች አጠናከረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዖዝያንም በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በርና በሸለቆው በር ቅጥሩም በዞረበት ማዕዘን አጠገብ ግንቦችን ሠርቶ መሸጋቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 26:9
10 Referencias Cruzadas  

ሐኖ​ንና የዘ​ናን ሰዎ​ችም የሸ​ለ​ቆ​ውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፥ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረጉ፤ ደግ​ሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚ​ሆን ቅጥር ሠሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ስን ልጅ አሜ​ስ​ያ​ስን በቤ​ት​ሳ​ሚስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር ከኤ​ፍ​ሬም በር ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ አራት መቶ ክንድ አፈ​ረሰ።


ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ እንደ ዓረባ ትሆናለች፣ እርስዋም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው በር ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።


“ከአ​ና​ም​ሄል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሠ​ራ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከማ​ዕ​ዘ​ኑም መውጫ ጀም​ረው እስከ በጎች በር ድረስ ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኞ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ሠሩ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የኢ​ን​ሓ​ዳድ ልጅ ባኒ ከዓ​ዛ​ር​ያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ እስከ ግን​ቡ​መ​ዞ​ሪያ ድረስ ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።


በሌ​ሊ​ትም በፈ​ፋው በኩል ወጥቼ ቅጥ​ሩን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ገባሁ፤ እን​ዲ​ሁም ተመ​ለ​ስሁ።


በሸ​ለ​ቆ​ውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለ​ስም ምን​ጭና ወደ ጕድፍ መጣ​ያው በር ሄድሁ፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ቅጥር፥ በእ​ሳ​ትም የተ​ቃ​ጠ​ሉ​ትን በሮ​ች​ዋን ተመ​ለ​ከ​ትሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios