ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
ነህምያ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወጣሁ። ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ አምላኬ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም አልነገርሁም፤ ከተቀመጥሁበት እንስሳ በቀር ከእኔ ጋራ ሌሎች እንስሳት አልነበሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊት ተነሣሁ፥ እኔና ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ ነገር ግን አምላኬ ለኢየሩሳሌም እንዳደርገው በልቤ ያስቀመጠውን ነገር ለማንም አልተናገርኩም። ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኢየሩሳሌም ስለማከናውነው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር ለእኔ የገለጠልኝን ምሥጢር ለማንም ሳልናገር ቈየሁ፤ ከዚያም በኋላ ከጓደኞቼ ጥቂቶቹን በማስከተል፥ በእኩለ ሌሊት ተነሥቼ ሄድኩ፤ የነበረን የጭነት እንስሳ እኔ የተቀመጥኩበት ብቻ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር አያሌ ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም። |
ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለስም ምንጭና ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ከእነርሱም እንዳልመለስ፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ “ልጄን ከግብጽ ጠራሁት” የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብጽ ሄደ፤ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።
እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።
ጌዴዎንም ከባሪያዎቹ ዐሥራ ሦስት ሰዎችን ወስዶ እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ የአባቱንም ቤተ ሰቦች፥ የከተማዉንም ሰዎች ስለፈራ ይህን በቀን ለማድረግ አልቻለም፤ ነገር ግን በሌሊት አደረገው።