ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮሐዳ፥ በዮሐናንና በያዱዕ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።
ነህምያ 12:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሌዋውያን ዘሮች መካከል እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ድረስ ያሉት የየቤተ ሰቡ ኀላፊዎች በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዊ ልጆች የአባቶች መሪዎች እስከ ኤልያሺብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተመዝግበው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ የሌዋውያን ቤተሰብ አለቆች በግልጽ መዝገብ የታወቁት የኤልያሺብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮናታን በሕይወት እስከ ኖረበት ዘመን ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ። |
ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮሐዳ፥ በዮሐናንና በያዱዕ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ።
የሌዋውያኑም አለቆች አሳብያ፥ ሰርብያ፥ ኢያሱ፥ የቀድምኤልም ልጆች፥ ወንድሞቻቸውም እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በእነርሱ ፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።