አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
ነህምያ 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዛኖህ፥ በዓዶላም፥ በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዛኖዋ፣ በዓዶላምና በመንደሮቻቸው፣ በለኪሶና በዕርሻዎቿ፣ በዓዜቃና በመንደሮቿ። ስለዚህ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ባለው ስፍራ ሁሉ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛኖሓ፥ ዓዱላምና በመንደሮቻቸው፥ ላኪሽና ሜዳዎችዋ፥ ዓዚቃና በመንደሮችዋ፤ እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዛኖሐ፥ በዐዱላምና በእነዚህም ከተሞች አጠገብ በሚገኙት መንደሮች ሁሉ ይኖሩ ነበር፤ ላኪሽና በአቅራቢያዋ የሚገኙ የእርሻ ቦታዎች፥ ዐዜቃና የአካባቢዋ መንደሮች ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ፤ በዚህ ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ መኖሪያ በደቡብ ከቤርሳቤህ፥ በሰሜን ከሂኖም ሸለቆ በመለስ ባለው ክልል ውስጥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጾርዓ፥ በየርሙት፥ በዛኖዋ በዓዶላም በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። |
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
የይስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይህ ነው፤ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው።
ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዲሠዋ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነበረውን ጣፌትን ርኩስ አደረገው።
ሐኖንና የዘናን ሰዎችም የሸለቆውን በር አደሱ፤ ሠሩት፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ፤ ደግሞም እስከ ጕድፍ መጣያ በር ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።
ስለዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ይሁዳን ወደ ኀጢአት እንዲያገቡት፥ ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን መሠዊያዎች ለበዓል ሠሩ።”
ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥
ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወጣል፤ ድንበሩም በሰሜን በኩል በራፋይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባሕር በኩል ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ይወጣል፤
ድንበሩም በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፤ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምንጭም ወረደ።