ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
ናሆም 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፣ ደጎብያ ተዘረጋ፥ በረረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማይ ከዋክብት እስኪበልጡ ድረስ፣ የነጋዴዎችሽን ቍጥር አበዛሽ፤ ምድሪቱን ግን እንደ አንበጣ ግጠው አሟጠጡ፤ ከዚያ በርረው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፤ አንበጣ ተዘረጋና በረረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነጋዴዎችሽ ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ በዝተዋል፤ ነገር ግን እንደ አንበጣ ምድሪቱን ግጠው በረው ይሄዳሉ። |
ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው።
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
በጢሮስ ላይ ይህን የመከረ ማን ነው? እርስዋ ከሁሉ የምትሻልና የምትበልጥ አይደለችምን? ነጋዴዎችዋ የከበሩ የምድር አለቆች ናቸው።
የሰማይን ሠራዊት መቍጠር፥ የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።”