ናሆም 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንግሥት ተገለጠች፥ ተማረከችም፥ ሴቶች ባሪያዎችዋም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣ አስቀድሞ ተነግሯል፤ ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤ ደረታቸውንም ይደቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዞቹ በሮች ተከፈቱ፥ ቤተ መንግሥቱም ቀለጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነነዌ ተዋረደች፤ ንግሥቲቱ ተማርካ ተወሰደች፤ ሴቶች አገልጋዮችዋ የርግብ ድምፅ የመሰለ የሐዘን ድምፅ ያሰማሉ፤ ደረታቸውንም እየመቱ ያለቅሳሉ። |
ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ፤ መብረርን እንደሚማር ርግብም በተራራ ላይ ይሆናሉ፤ እኔም በኀጢአታቸው ሁሉ እገድላለሁ።