Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ናሆም 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ነነዌ ተዋረደች፤ ንግሥቲቱ ተማርካ ተወሰደች፤ ሴቶች አገልጋዮችዋ የርግብ ድምፅ የመሰለ የሐዘን ድምፅ ያሰማሉ፤ ደረታቸውንም እየመቱ ያለቅሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣ አስቀድሞ ተነግሯል፤ ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤ ደረታቸውንም ይደቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የወንዞቹ በሮች ተከፈቱ፥ ቤተ መንግሥቱም ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ንግሥት ተገለጠች፥ ተማረከችም፥ ሴቶች ባሪያዎችዋም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ ዋይ ዋይ ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 2:7
9 Referencias Cruzadas  

ሁላችንም እንደ ድብ በመጮኽ እንደ ርግብም ምርር ብለን በማልቅስ ፍትሕንና መዳንን ለማግኘት እንጠባበቃለን፤ እነርሱ ግን ከእኛ የራቁ ስለ ሆኑ አይገኙም።


እንደ ሽመላ እጮኽ ነበር፤ እንደ ርግብ የሐዘን ድምፅ አሰማ ነበር፤ ወደ ሰማይም አሻቅቤ ከመመልከቴ የተነሣ፥ ዐይኖቼ በጣም ደክመው ነበር። ጌታ ሆይ! እባክህን ከዚህ ሁሉ መከራ አድነኝ!


ነገሩን ለመመልከት እዚያ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎች ሁሉ የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ በማዘን ደረታቸውን እየመቱ ወደየቤታቸው ተመለሱ።


ብዙ ሰዎችም ኢየሱስን ይከተሉ ነበር፤ ከእነርሱም መካከል ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱለት ሴቶች ነበሩ።


ደስ የሚያሰኘው ለሙ መሬትና የወይን ቦታ ሁሉ ስለ ጠፋ ደረታችሁን እየደቃችሁ አልቅሱ።


ጴጥሮስ ከካህናት አለቃው ቤት በታች በግቢው ውስጥ እንዳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንድዋ መጣች፤


የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ።


በወንዙ በኩል ያሉት የከተማይቱ ቅጽር በሮች ወለል ብለው ተከፈቱ፤ ቤተ መንግሥቱም በሽብር ተሞላ።


ወታደሮችሽ ሁሉ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል፤ የጠረፍሽ በሮች ለጠላቶችሽ ክፍት ሆነዋል፤ መወርወሪያዎቹም እሳት በልቶአቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios