አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ።
ናሆም 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ላይ የምታስቡት ምንድር ነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋል፥ መከራም ሁለተኛ አይነሣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ላይ ምንም ቢያሤሩ፣ እርሱ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ላይ የምታስቡት ምንድነው? እርሱ ፍጻሜ ያደርጋል፥ መከራም ዳግመኛ አይነሣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእግዚአብሔር ላይ የምታሤሩት ለምንድን ነው? እርሱ እናንተን እስከ መጨረሻው ይደመስሳችኋል፤ ዳግመኛም በእርሱ ላይ መነሣሣት ከቶ አትችሉም። |
አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ።
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።
አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።
ልብ ሁሉ ይማረክ ዘንድ ኅሊናም ለክርስቶስ ይገዛ ዘንድ በእግዚአብሔር ላይ የሚታበየውንና ከፍ ከፍ የሚለውን እናፈርሳለን።
አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አሁንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከምድር ጋር ላጣብቀው፤ ሁለተኛም አልደግመውም” አለው።