ሚክያስ 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፋት ቤት ሆይ፤ በግፍ የተገኘ ሀብታችሁን፣ በሐሰተኛ መስፈሪያ የሰበሰባችሁትን አስጸያፊ ነገር እረሳዋለሁን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉ ቤት የክፋት መዝገብ፥ አስጸያፊ ሐሰተኛ መስፈሪያ አሁንም አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኛ በቤቱ በክፋት የሰበሰበውን ሀብትና የተረገመውን ሐሰተኛ ሚዛን ልረሳቸው እችላለሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን? |
በፋርስ ሀገሮችና በግብፅ ሀገሮች ዐውጁና፥ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ተአምር፥ በመካካልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ” በሉ።
እኔም፦ ምንድር ናት? አልሁ። እርሱም፦ ይህች የምትወጣው የኢፍ መስፈሪያ ናት አለኝ። ደግሞም፦ በምድር ሁሉ ላይ ያለ በደላቸው ይህ ነው አለ።
የእስራኤል ልጆች ግን እርም በሆነው ነገር ታላቅ በደል በደሉ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ እርም ከሆነው ነገር ወሰደ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች ላይ ተቈጣ።