ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እንሄዳለን፤ በጎዳናም እንውላለን፤ ወደ ጌታችን ወደ ሴይር እስክንደርስም በሕፃናቱ ርምጃ መጠን እንሄዳለን” አለው።
ማቴዎስ 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ ቍራጭ ጨርቅ የሚጥፍ ሰው የለም፤ ይህ ከሆነ አዲሱ ዕራፊ ካረጀው ልብስ ላይ ተቦጭቆ ቀዳዳውን የባሰ ያሰፋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ ቀዳዳውም የባሰ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ ዕራፊ የሚጥፍ ማንም የለም፤ ቢጣፍ ግን አዲሱ ዕራፊ አሮጌውን ልብስ ቦጭቆ ቀዳዳውን የባሰ ያሰፋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። |
ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እንሄዳለን፤ በጎዳናም እንውላለን፤ ወደ ጌታችን ወደ ሴይር እስክንደርስም በሕፃናቱ ርምጃ መጠን እንሄዳለን” አለው።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፤ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።”
በምሳሌም እንዲህ አላቸው፥ “በአሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአዲስ ልብስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ ያለዚያ ግን አዲሱ አሮጌውን ይቀድደዋል፤ አዲሱ እራፊም ከአሮጌው ጋር አይስማማም።
ይህቺ የዚህ ሥራ አገልግሎት ግዳጅ የምትፈጽመው ለዚህ ለቅዱሳን ችግር መሟላት ብቻ አይደለም፤ በቅዱሳን ዘንድም ደግሞ የእግዚአብሔርን ምስጋና ታበዛለች።