ማቴዎስ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ የዮሐንስን መታሰር በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ዮሐንስ እንደታሰረ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ የዮሐንስን መታሰር በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ምድር ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ። |
እርሱም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ወሰደው፤ ጌታችን ኢየሱስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባላለህ፤” አለው፤ ትርጓሜውም ጴጥሮስ ማለት ነው።
ጌታችን ኢየሱስም በቃና ዘገሊላ ያደረገው የተአምራት መጀመሪያ ይህ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት።