Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 1:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እር​ሱም ወደ ጌታ​ችን ወደ ኢየ​ሱስ ወሰ​ደው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስም​ዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባ​ላ​ለህ፤” አለው፤ ትር​ጓ​ሜ​ውም ጴጥ​ሮስ ማለት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 በማግስቱም፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አግኝቶ፣ “ተከተለኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 በማግስቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ!” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ፦ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 1:43
19 Referencias Cruzadas  

ያል​ፈ​ለ​ጉኝ አገ​ኙኝ፤ ላል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ኘሁ፤ ስሜን ላል​ጠራ ሕዝብ፥ “እነ​ሆኝ” አል​ሁት።


ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥


ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ።


ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው።


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


የሰው ልጅ የጠ​ፋ​ውን ሊፈ​ል​ግና ሊያ​ድን መጥ​ቶ​አ​ልና።”


ዮሐ​ንስ ያጠ​ም​ቅ​በት በነ​በ​ረው በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በቢ​ታ​ንያ በቤተ ራባ እን​ዲህ ሆነ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ደግሞ ዮሐ​ንስ ከሁ​ለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፥


ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ ሲል ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ተከ​ተ​ሉት።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ወደደ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም አገ​ኘ​ውና “ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


እነ​ር​ሱም ከገ​ሊላ፥ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊል​ጶስ ሄደው፥ “አቤቱ፥ ጌታ ኢየ​ሱ​ስን ልና​የው እን​ወ​ድ​ዳ​ለን” ብለው ለመ​ኑት።


ፊል​ጶ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳ​የ​ንና ይበ​ቃ​ናል” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊል​ጶ​ስን፥ “ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች የም​ና​በ​ላ​ቸው እን​ጀራ ከወ​ዴት እን​ግዛ?” አለው።


ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።”


ነገር ግን ይህን ፈጽሜ የተ​ቀ​በ​ልሁ አይ​ደ​ለም፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ እኔን የመ​ረ​ጠ​በ​ትን አገኝ ዘንድ እሮ​ጣ​ለሁ እንጂ።


እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos