“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በአሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ። ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦
ማቴዎስ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘አብርሃም አባት አለን’ በማለት አታስቡ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልባችሁ ‘አብርሃም አባት አለን’ ብላችሁ አታስቡ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልባችሁም፦ አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና፦ ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል። |
“የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ምድር በአሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙዎች ነን፤ ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ። ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦
‘አባት አብርሃም ሆይ፥ እዘንልኝ፤ በዚች እሳት እጅግ ተሠቃይቻለሁና፥ ጣቱን ከውኃ ነክሮ ምላሴን ያቀዘቅዝልኝ ዘንድ አልዓዛርን ላከው’ ብሎ ተጣራ።
እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።”
እነርሱም መልሰው፥ “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማንም ከቶ ባሮች አልሆንም፤ እንግዲህ እንዴት አርነት ትወጣላችሁ ትለናለህ?” አሉት።
“እናንተ ከአብርሃም ወገን የተወለዳችሁ ወንድሞቻችን እግዚአብሔርንም የምትፈሩ፥ ይህ የሕይወት ቃል ለእናንተ ተልኮአል።
ስምዖንም፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ አሕዛብን ይቅር እንዳላቸውና ከውስጣቸውም ለስሙ ሕዝብን እንደ መረጠ ተናግሮአል።