መሎጊያዎቹም ረጃጅሞች ነበሩና በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ከመቅደሱ ውስጥ ጫፎቻቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።
ማቴዎስ 27:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተባለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ያ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተብሎ ይጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ምክንያት ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” እየተባለ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። |
መሎጊያዎቹም ረጃጅሞች ነበሩና በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ከመቅደሱ ውስጥ ጫፎቻቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።
በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ዜናዉ ተሰማ፤ ያም መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ይኸውም የደም መሬት ማለት ነው።
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።
ሰውየውም ወደ ኬጤዎናውያን ምድር ሄደ፤ በዚያም ከተማን ሠራ፤ ስምዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት። እስከ ዛሬም ድረስ ስምዋ ያው ነው።