ማቴዎስ 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መንግሥተ ሰማይ ለልጁ ሰርግ የደገሰን ንጉሥ ትመስላለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “መንግሥተ ሰማይ ለልጁ የሠርግ ድግስ የደገሰውን ንጉሥ ትመስላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች። |
እናንተም፥ በመጣና በር በመታ ጊዜ ወዲያው ይከፍቱለት ዘንድ ከሰርግ እስኪመለስ ጌታቸውን እንደሚጠብቁ ሰዎች ሁኑ።
ለእግዚአብሔር የሚገባ ቅንዐት እቀናላችኋለሁና፤ ወደ እርሱ አቀርባችሁ ዘንድ ለአንዱ ንጹሕ ድንግል ሙሽራ ለክርስቶስ አጭቻችኋለሁና።
ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ እንደ ነገሩህ ቃል ታደርጋለህ፤ ያስተማሩህንም ሕጉን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።