እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ።
ማቴዎስ 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች፤ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄሮድስ የልደቱን ቀን ሲያከብር፣ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን ደስ ስላሠኘችው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሄሮድስ የልደት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ጨፈረች፥ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሄሮድስ ልደት በሚከበርበት ቀን የሄሮድያዳ ልጅ መጥታ በተጋባዦች መካከል እየጨፈረች ሄሮድስን አስደሰተች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን ፈርዖን የተወለደበት ዕለት ነበር፤ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ፤ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ዐሰበ።
ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በዐሥራ አምስት ዓመት ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮድስም በገሊላ የአራተኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወንድሙ ፊልጶስም የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አራተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳንዮስም የሳብላኒስ አራተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥
ዮሐንስም የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሄሮድስ ያደርገው ስለነበረው ክፉ ነገር ሁሉ ይገሥጸው ነበር።
በቀባኸው በቅዱስ ልጅህ ላይ ሄሮድስና ጰንጤናዊው ጲላጦስ ከወገኖቻቸውና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በእውነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።