ማቴዎስ 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቡ ልብ ደንድኗልና፤ ጆሯቸውም አይሰማም፤ እንዳያዩም ዐይናቸውን ጨፍነዋል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው፣ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኋቸው ነበር።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፥ ጆሮአቸው ደንቁሮአል፥ ዓይናቸውም ተጨፍኖአል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸው ተደፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍነዋል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸውም ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኳቸው ነበር።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል። |
እንግዲህ ልባቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእነርሱም ነፍሱን ለማዳን የሚችል ማንም እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚልም እንደሌለ ተመልከቱ።
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
“ከዳተኞች ልጆች ሆይ! ተመለሱ፤ ቍስላችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ እኛ አገልጋዮችህ እንሆናለን፤ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና።
እነሆ ፈውስንና መድኀኒትን እሰጣታለሁ፤ እፈውሳታለሁም፤ የሰላምንና የእውነትንም መንገድ እገልጥላቸዋለሁ።
አሦር አያድነንም፤ በፈረስም ላይ አንቀመጥም፤ ድሃአደጉም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ የእጆቻችንን ሥራ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም።”
ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።
በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ወደ እኔም እንዳይመለሱና ይቅር እንዳልላቸው የዚህ ሕዝብ ልባቸው ደንድኖአልና፥ ጆሮአቸውም ደንቁሮአልና፥ ዐይናቸውንም ጨፍነዋልና’።