በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ማቴዎስ 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ፤ ዋይ ዋይም አላላችሁም’ ይሉአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ አላለቀሳችሁም’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ አልጨፈራችሁም፥ ሙሾ አወረድንላችሁ አላለቀሳችሁም’ ይሉአቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ አልጨፈራችሁም! ሙሾ አወረድንላችሁ አላለቀሳችሁም!’ የሚሉትን ልጆች ይመስላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንቢልታ ነፋንላችሁ ዘፈንም አልዘፈናችሁም ሙሾ አወጣንላችሁ ዋይ ዋይም አላላችሁም ይሉአቸዋል። |
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፤ ከበሮንና መሰንቆንም መቱ፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፤ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።
በዐልን እንደሚያከብሩ፥ ሁልጊዜ ደስ ሊላችሁ፥ ወደ ተቀደሰው ቦታየም ልትሄዱ አይገባችሁምን? በእግዚአብሔር ተራራ ደስ እንደሚላቸው በእንቢልታ ወደ እስራኤል ቅዱስ ልትሄዱ ይገባችኋል።
የእስራኤል ድንግል ሆይ እንደ ገና እሠራሻለሁ፤ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ትወጫለሽ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
በገበያ ተቀምጠው ባልንጀሮቻቸውን ጠርተው፥ “አቀነቀንላችሁ፥ አልዘፈናችሁምም፤ ሙሾም አወጣንላችሁ፥ አላለቀሳችሁምም የሚሉአቸው ልጆችን ይመስላሉ።
ሁሉም እያለቀሱ ዋይ ዋይ ይሉላት ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስ ግን፥ “አታልቅሱ፤ ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።