ማርቆስ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፤ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና “እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም፤” ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ተነሥቶ ሁሉም እያዩት ዐልጋውን ተሸክሞ ሄደ፤ በስፍራው የነበሩትም ሁሉ በሁኔታው በመደነቅ፣ “የዚህ ዐይነት ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም!” በማለት ለእግዚአብሔር ምስጋና አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ተነሥቶ ሁሉም እያዩት ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ ሄደ፤ ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም፤” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽባውም ወዲያውኑ ተነሣና አልጋውን ተሸክሞ በሰዎቹ ሁሉ ፊት ወጣ። ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አይተን አናውቅም እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣ፥ ስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙና፦ እንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ። |
ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።
ሁሉም ፈሩ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነሣልን፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐብኝቶአልና።”
ከሕዝቡም ብዙዎች አመኑበትና፥ “በውኑ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው ተአምራት የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።
እነርሱንም የሚቀጡበት ምክንያት ስለ አጡባቸው ገሥጸው ለቀቁአቸው፤ ስለ ተደረገው ተአምር ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበርና።