በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
ማርቆስ 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እባቦችን ይይዛሉ፤የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይድናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እባቦችን በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውንም በሕመምተኞች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይፈወሳሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እባቦችን በእጃቸው ይይዛሉ፤ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውንም በሕመምተኞች ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱም ይፈወሳሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እባቦችን ቢይዙ፥ ወይም የሚገድል መርዝ እንኳ ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በበሽተኞች ላይ ሲጭኑ በሽተኞቹ ይድናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ። |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኀይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጐዳችሁም ነገር የለም።
ከልብሱ ዘርፍና ከመጠምጠሚያዉ ጫፍ ቈርጠው እየወሰዱ በድውያኑ ላይ ያኖሩት ነበር፤ እነርሱም ይፈወሱ ነበር፤ ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
ጴጥሮስም ሕዝቡን ባያቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፥ “እናንት የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደንቃላችሁ? እኛንስ በኀይላችንና በጽድቃችን ይህን ሰው በእግሩ እንዲሄድ እንዳደረግነው አስመስላችሁ ለምን ታዩናላችሁ?
ስሙን በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፤ እርሱንም በማመን በፊታችሁ ይህን ሕይወት ሰጠው።
እንግዲህ እናንተ ሁላችሁ፥ የእስራኤልም ወገን ሁሉ፥ እናንተ በሰቀላችሁት፥ እግዚአብሔርም ከሙታን ለይቶ በአስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊታችሁም እንደ ቆመ በርግጥ ዕወቁ።
በቅዱሱ ልጅህም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕሙማንን ትፈውስ ዘንድ ተአምራትንና ድንቅ ሥራንም ታደርግ ዘንድ እጅህን ዘርጋ።”
የሰላም አምላክም ፈጥኖ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ይቀጥቅጠው፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።