Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 9:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይፈ​ው​ስህ፤ ተነ​ሥና አል​ጋ​ህን አን​ጥፍ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ተነሣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ጴጥሮስም፣ “ኤንያ ሆይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣና መኝታህን አንጥፍ” አለው። ኤንያም ወዲያውኑ ብድግ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ጴጥሮስም “ኤንያ ሆይ! ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ፤” አለው። ወዲያውም ተነሣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ጴጥሮስም “ኤኒያ ሆይ! ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሥና አልጋህን አንጥፍ!” አለው፤ እርሱም ወዲያውኑ ተነሣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ጴጥሮስም፦ “ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 9:34
11 Referencias Cruzadas  

እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እወዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።


ነገር ግን በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


ብዙ ቀንም እን​ዲሁ ታደ​ርግ ነበር፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አሳ​ዘ​ነ​ችው፤ መለስ ብሎም፥ “መን​ፈስ ርኩስ፥ ከእ​ር​ስዋ እን​ድ​ት​ወጣ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ” አለው፤ ወዲ​ያ​ው​ኑም ተዋት።


ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?


ስሙን በማ​መን ይህን የም​ታ​ዩ​ት​ንና የም​ታ​ው​ቁ​ትን የእ​ርሱ ስም አጸ​ናው፤ እር​ሱ​ንም በማ​መን በፊ​ታ​ችሁ ይህን ሕይ​ወት ሰጠው።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ወር​ቅና ብር የለ​ኝም፤ ያለ​ኝን ግን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ እነሆ፥ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተነ​ሥ​ተህ ሂድ” አለው።


እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ።


በዚ​ያም ኤንያ የተ​ሰኘ ሰውን አገኘ፤ እር​ሱም ታሞ በአ​ልጋ ከተኛ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ሽባ ነበ​ርና።


በል​ዳና በሳ​ሮና የሚ​ኖ​ሩም ሁሉ እር​ሱን አይ​ተው ወደ ጌታ​ችን ተመ​ለሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos