ማርቆስ 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያምኑትን እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ልሳንም ይናገራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያምኑትን እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ልሳንም ይናገራሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ የሚያምኑ ሁሉ እነዚህን ተአምራት ያደርጋሉ፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋም ይናገራሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ |
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።
ብዙ ቀንም እንዲሁ ታደርግ ነበር፤ ጳውሎስንም አሳዘነችው፤ መለስ ብሎም፥ “መንፈስ ርኩስ፥ ከእርስዋ እንድትወጣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝዤሃለሁ” አለው፤ ወዲያውኑም ተዋት።
ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ፤ ያንጊዜም በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ።
አሁን ግን በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ከአብ ገንዘብ አድርጎ ይህን ዛሬ የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።
ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከአሉ ከተሞች ብዙዎች ይመጡ ነበር፤ የታመሙትንና ክፉዎች አጋንንት የያዙአቸውንም ያመጡ ነበር፥ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።
ርኩሳን መናፍስት ያደሩባቸውም ብዙዎች ነበሩና፥ በታላቅ ቃል እየጮኹ ይወጡ ነበር፤ ብዙዎች ልምሾዎችና አንካሶችም ይፈወሱ ነበር።
ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል።
እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም መምህራንን፥ ከዚህም በኋላ ተአምራትና ኀይል ማድረግ የተሰጣቸውን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመርዳትም ሀብት የተሰጣቸውን፥ የመምራትና ቋንቋን የመናገር ሀብት የተሰጣቸውን ነው።
የሰውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመላእክትንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌለኝ እንደሚጮህ ነሐስ፥ ወይም እንደሚመታ ከበሮ መሆኔ ነው።
በቋንቋ የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው የሚናገር አይደለም። የሚናገረውን የሚሰማው የለምና፥ ነገር ግን በመንፈስ ምሥጢርን ይናገራል።