እርሱ ግን በመከራው ጊዜ አፉን አልከፈተም፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
ማርቆስ 15:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናት አለቆችም በብዙ ነገር ከሰሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናት አለቆችም በብዙ ነገር ከሰሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካህናት አለቆች ግን ኢየሱስን በብዙ ይወነጅሉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም። |
እርሱ ግን በመከራው ጊዜ አፉን አልከፈተም፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
ስለዚህም ጲላጦስ ሊፈታው ወድዶ ነበር፤ አይሁድ ግን፥ “ይህን ከፈታኸው የቄሣር ወዳጅ አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሰው ሁሉ በቄሣር ላይ የሚያምፅ ነውና” ብለው ጮሁ።