በቀትርም ጊዜ ቴስብያዊው ኤልያስ፥ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት ይጫወት ይሆናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል” እያለ ይዘባበትባቸው ጀመር።
ማርቆስ 14:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛም መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ ይበቃል፤ ሰዓቲቱ ደረሰች፤ እነሆ፥ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስተኛ ጊዜም መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም እንደ ተኛችሁና እንዳረፋችሁ ናችሁ? ይበቃል! ሰዓቲቱ ደርሳለች፤ እነሆ፤ የሰው ልጅ ለኀጢአተኞች እጅ ዐልፎ ይሰጣል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስተኛ ጊዜም መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም እንደተኛችሁና እንዳረፋችሁ ናችሁ? ይበቃል ሰዓቲቱ ደርሳለች፤ እነሆ፤ የሰው ልጅ ለኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስተኛም ጊዜ ወደ እነርሱ መጥቶ፥ እንዲህ አላቸው፦ “አሁንም ገና ተኝታችኋልን? አሁንም ዕረፍት ታደርጋላችሁን? እንግዲህስ በቃ! ሰዓቱ ደርሶአል! እነሆ! የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስተኛም መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ ይበቃል፤ ሰዓቲቱ ደረሰች፤ እነሆ፥ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። |
በቀትርም ጊዜ ቴስብያዊው ኤልያስ፥ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት ይጫወት ይሆናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል” እያለ ይዘባበትባቸው ጀመር።
ወደ ንጉሡም ደረሰ። ንጉሡም፥ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንሂድን? ወይስ እንቅር?” አለው። እርሱም፥ “ውጣና ተከናወን፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል” ብሎ መለሰለት።
ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባትህ ነቢያትና ወደ እናትህ ነቢያት ሂድ፥” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ፥ “አይደለም፤ በሞዓብ እጅ ይጥላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን ሦስት ነገሥታት ጠርቶአልን?” አለው።
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ ኀጢአታችሁን ተዉ፤ ከዚህ በኋላ ስሙኝ፤ ቅዱሱን ስሜንም ከእንግዲህ ወዲህ በኀጢአታችሁና በመባችሁ አታርክሱ።
“አሁንስ ነፍሴ ታወከች፤ ግን ምን እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍሴን አድናት፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደርሻለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ተናግሮ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤
ጌታችን ኢየሱስም በቤተ መቅደስ ሲያስተምራቸው በሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ይህን ተናገራቸው፤ ነገር ግን አልያዙትም፤ ጊዜው ገና አልደረሰም ነበርና።
አባቶቻችሁ ከነቢያት ያላሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው።