ማርቆስ 14:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “እውነት እልሃለሁ፤ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም፥ “እውነት እልሃለሁ፤ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ፥ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “በእውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው። |
እግዚአብሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሁለተኛም ቀን ሆነ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ነፍስህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ዶሮ አይጮህም።
በረኛዪቱ አገልጋይም፥ “አንተም ከዚያ ሰው ደቀ መዛሙርት ወገን አይደለህምን?” አለችው፤ እርሱም፥ “አይደለሁም” አላት።