Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ሁለ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ሁለተኛ ቀን ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራዉ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ሁሉተኚ ቀን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 1:8
11 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያ​ው​ንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ።


ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ። ሦስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አራ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አም​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃ​ኑን “ቀን፥” ጨለ​ማ​ው​ንም “ሌሊት” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ አን​ደኛ ቀንም ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠፈ​ርን አደ​ረገ፤ ከጠ​ፈር በላ​ይና ከጠ​ፈር በታች ያሉ​ት​ንም ውኆች ለየ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃ በአ​ንድ ስፍራ ይሰ​ብ​ሰብ፥ የብ​ሱም ይገ​ለጥ አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ። ከሰ​ማይ በታች ያለው ውኃም በመ​ጠ​ራ​ቀ​ሚ​ያው ተሰ​በ​ሰበ፤ የብ​ሱም ተገ​ለጠ።


ወን​ድና ሴት አድ​ርጎ ፈጠ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም። እነ​ር​ሱ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት ቀን ስሙን አዳም ብሎ ጠራው።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብረ​ሳሽ፥ ቀኜ ትር​ሳኝ።


ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos