ማርቆስ 10:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ!” ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፥ “የዳዊት ልጅ፥ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ” እያለ ይጮኽ ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የሚያልፈው የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ባወቀ ጊዜ “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ እባክህ ራራልኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ፦ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር። |
እርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ! የእግዚአብሔር ቅዱሱ!” ብሎ ጮኸ።
ፊልጶስም ናትናኤልን አገኘውና፥ “ሙሴ በኦሪት፥ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው” አለው።
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”