Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ናዝሬት ወደምትባል ከተማም ሄዶ መኖር ጀመረ። በዚህም በነቢያት፣ “ናዝራዊ ይባላል” ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው እንዲፈጸም፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ናዝራዊ ይባላል” ተብሎ በነቢያት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 2:23
20 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ትፀ​ን​ሻ​ለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ልጁም ከእ​ናቱ ማኅ​ፀን ጀምሮ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለየ ናዝ​ራዊ ይሆ​ና​ልና በራሱ ላይ ምላጭ አይ​ድ​ረ​ስ​በት፤ እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ማዳን ይጀ​ም​ራል።”


እርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ! የእግዚአብሔር ቅዱሱ!” ብሎ ጮኸ።


ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፤” አለች።


በነቢይ ከጌታ ዘንድ፥


ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል።


“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።


ጲላ​ጦ​ስም ጽሕ​ፈት ጽፎ በመ​ስ​ቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ” የሚል ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ደ​ገና፥ “ማንን ትሻ​ላ​ችሁ?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን” አሉት።


“የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን” ብለው መለ​ሱ​ለት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ ነኝ” አላ​ቸው፤ አሳ​ልፎ የሰ​ጠው ይሁ​ዳም በዚ​ያው አብ​ሮ​አ​ቸው ቆሞ ነበር።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ከፈ​ጸሙ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ ከተ​ማ​ቸው ወደ ናዝ​ሬት ተመ​ለሱ።


በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ውም ወር መል​አኩ ገብ​ር​ኤል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ስሟ ናዝ​ሬት ወደ​ም​ት​ባ​ለው ወደ አን​ዲት የገ​ሊላ ከተማ ከዳ​ዊት ወገን ለሚ​ሆን ዮሴፍ ለሚ​ባል ሰው ወደ ታጨ​ችው ወደ አን​ዲት ድን​ግል ተላከ፤


“የተ​ሳ​ለው ሰው ሕግ ይህ ነው፤ የስ​እ​ለቱ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ራሱ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ይቅ​ረብ፤ ቍር​ባ​ኑ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ።


እር​ስ​ዋም፥ “አዶ​ናይ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! የባ​ር​ያ​ህን መዋ​ረድ ተመ​ል​ክ​ተህ ብታ​ስ​በኝ፥ ለባ​ር​ያ​ህም ወንድ ልጅ ብት​ሰጥ ዕድ​ሜ​ውን ሁሉ ለአ​ንተ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክር መጠ​ጥም አይ​ጠ​ጣም። ምላ​ጭም በራሱ ላይ አይ​ደ​ር​ስም” ብላ ስእ​ለት ተሳ​ለች።


ሕዝቡም “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው፤” አሉ።


በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።


እነ​ር​ሱም፥ “የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ያል​ፋል” ብለው ነገ​ሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios