ማርቆስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ልጅ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ልጅ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ። |
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
ናትናኤልም፥ “በየት ታውቀኛለህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ በበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይችሃለሁ” አለው።
ነገር ግን ይህ የተጻፈ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እናንተ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ የዘለዓለም ሕይወትን ታገኙ ዘንድ ነው።
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲህ ወዶታልና።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤዉ ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።”
ስለ ሥጋ ደካማነት የኦሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተሳነው ጊዜ እግዚአብሔር በኀጢኣተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያችንም ኀጢአት በሥጋው ቀጣት።