እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
ሉቃስ 7:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ አለው፥ “ለአንድ አበዳሪ ሁለት ባለ ዕዳዎች ነበሩት፤ በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት፤ በሁለተኛውም አምሳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንደኛው ዐምስት መቶ ዲናር፣ ሁለተኛው ደግሞ ዐምሳ ዲናር ነበረበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት፤ አንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት፤ ሌላው ደግሞ አምሳ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ አንዱ አምስት መቶ ዲናር ሌላው ደግሞ ኀምሳ ዲናር ተበደሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም።
እርሱ ግን መልሶ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። “ሄደን እንጀራ በሁለት መቶ ዲናር እንግዛላቸውን? እንዲበሉም እንስጣቸውን?” አሉት።
እኛም የበደለንን ሁሉ ይቅር እንድንል በደላችንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ።”
ወይስ እነዚያ በሰሊሆም ግንብ ተጭኖ የገደላቸው ዐሥራ ስምንቱ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ሰዎች ይልቅ ተለይተው ኀጢእታኞች ይመስሉአችኋልን?
ስለዚህም እልሃለሁ፤ ብዙ ኀጢኣቷ ተሰርዮላታል፤ በብዙ ወድዳለችና፤ ጥቂት የሚወድድ ጥቂት ይሰረይለታል፤ ብዙ የሚወድድም ብዙ ይሰረይለታል።”