Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወይስ እነ​ዚያ በሰ​ሊ​ሆም ግንብ ተጭኖ የገ​ደ​ላ​ቸው ዐሥራ ስም​ንቱ ሰዎች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎች ይልቅ ተለ​ይ​ተው ኀጢ​እ​ታ​ኞች ይመ​ስ​ሉ​አ​ች​ኋ​ልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወይም ደግሞ በሰሊሆም ግንብ ተንዶባቸው የሞቱት ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ በደለኞች ስለ ነበሩ ይመስላችኋል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወይንስ በሰሊሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው ስለሞቱት ዐሥራ ስምንት ሰዎች ምን ታስባላችሁ? እነርሱ በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሰዎች ሁሉ የባሱ ኃጢአተኞች የነበሩ ይመስሉአችኋልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 13:4
13 Referencias Cruzadas  

የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ።


እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


“እኒህ ሕዝብ በቀ​ስታ በሚ​ሄ​ደው በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ቍርጥ ምክ​ርን መከሩ፤ ረአ​ሶ​ን​ንና የሮ​ሜ​ል​ዩን ልጅ ያነ​ግ​ሡ​ላ​ቸው ዘንድ ይወ​ዳ​ሉና።


መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ።


እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


እኛም የበ​ደ​ለ​ንን ሁሉ ይቅር እን​ድ​ንል በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታ​ግ​ባን፤ ከክፉ ሁሉ አድ​ነን እንጂ።”


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።


አይ​ደ​ለም፤ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ንስሓ ካል​ገ​ባ​ችሁ ሁላ​ችሁ እንደ እነ​ርሱ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


እር​ሱም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ የሚ​ባ​ለው ሰው በም​ራቁ ጭቃ አድ​ርጎ ዐይ​ኖ​ችን ቀባ​ኝና ሂደህ በሰ​ሊ​ሆም ውኃ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄም ታጠ​ብ​ሁና አየሁ” አላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሂድና በሰ​ሊ​ሆም መጠ​መ​ቂያ ታጠብ” ትር​ጓ​ሜ​ውም የተ​ላከ ማለት ነው፤ ሄዶም ታጠ​በና እያየ ተመ​ለሰ።


አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos