እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
ሉቃስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ኀጢአት ስርየት ለንስሓ የሚያበቃ ጥምቀትን እየሰበከ በዮርዳኖስ አውራጃ ዞረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ለኀጢአት ስርየት የሚሆን የንስሓን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ወንዝ አካባቢ ወዳሉት ስፍራዎች ሁሉ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዮርዳኖስም ዙርያ ወዳለው አገር ሁሉ መጥቶ ለኃጢአት ስርየት የንስሓን ጥምቀት ሰበከ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዮሐንስ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ባሉት አገሮች ሁሉ እየተዘዋወረ፦ “ለኃጢአታችሁ ይቅርታ እንድታገኙ ንስሓ ገብታችሁ ተጠመቁ፤” እያለ ያስተምር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ፦ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ። |
እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
ወደ ዮሐንስም ሄደው፥ “መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነበረው፥ አንተም የመሰከርህለት እርሱ እነሆ፥ ያጠምቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄዳል” አሉት።
ጳውሎስም፥ “ዮሐንስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ እየሰበከ የንስሓ ጥምቀትን አጠመቀ” አላቸው።