እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?
ሉቃስ 23:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር፤ አለቆችም፥ “ሌሎችን አዳነ፤ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌዙበት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። ገዦችም፣ “ሌሎችን አዳነ፤ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ እርሱ ከሆነ፣ እስኪ ራሱን ያድን” እያሉ አፌዙበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። መኰንኖቹም “ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ፥ ራሱን ያድን፤” እያሉ ያፌዙበት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ቆሞ ይመለከት ነበር፤ የአይሁድ አለቆችም “ሌሎችንስ አዳነ እንግዲህ እርሱ የተመረጠው የእግዚአብሔር መሲሕ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን!” እያሉ ያፌዙበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። መኳንንቱም ደግሞ፦ ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ፥ ራሱን ያድን እያሉ ያፌዙበት ነበር። |
እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
አብረው ተሰቅለው ከነበሩት አንዱ ወንበዴ፥ “አንተስ ክርስቶስ ከሆንህ ራስህን አድን፤ እኛንም አድነን” ብሎ ተሳደበ።