ሉቃስ 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር አቃለለው፤ አፌዘበትም፤ የሚያንፀባርቅ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄሮድስም ከወታደሮቹ ጋራ ናቀው፤ አፌዙበትም፤ የክብር ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው፤ አፌዘበትም፤ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄሮድስም ከጭፍሮቹ ጋር ሆኖ በንቀት አፌዘበት፤ ጌጠኛ ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው ዘበተበትም፥ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። |
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ጌታችን ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐናጸፊያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላጦስም፥ “እነሆ፥ ሰውዬው” አላቸው።
የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ “አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ድኻውንም “አንተስ ወደዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?