ሉቃስ 20:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምጥተውም አሳዩት፤ “መልኩ፥ ጽሕፈቱስ የማነው?” አላቸው፤ እነርሱም፥ “የቄሣር ነው” ብለው መለሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስኪ አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ በላዩ ያለው የማን መልክና ጽሕፈት ነው?” እነርሱም፣ “የቄሳር ነው” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ዲናር አሳዩኝ፤ መልኩና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። ሲመልሱም “የቄሣር ነው” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስቲ ገንዘቡን አሳዩኝ፤ በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” እነርሱም “የሮም ንጉሠ ነገሥት ነው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልኩ ጽሕፈቱስ የማን ነው? አላቸው። መልሰውም፦ የቄሣር ነው አሉት። |
እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄሣር ግብር እንዳይሰጡ ሲከለክልና ሕዝቡን ሲያሳምፅ፥ ራሱንም የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስን ሲያደርግ አገኘነው።”
ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በዐሥራ አምስት ዓመት ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮድስም በገሊላ የአራተኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወንድሙ ፊልጶስም የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አራተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳንዮስም የሳብላኒስ አራተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥
ከመካከላቸውም አጋቦስ የተባለ አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እንደሚመጣ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ተናገረ፤ ይህም በቄሣር ቀላውዴዎስ ዘመን ሆነ።