አሁንም ይህች ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንደማይሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መንግሥትን ይጐዳል።
ሉቃስ 20:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቄሣር ግብር መስጠት ይገባል? ወይስ አይገባም?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ለቄሳር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቄሣር ግብር እንድንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስቲ ንገረን! በሕጋችን መሠረት ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር መክፈል ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቄሣር ግብር ልንሰጥ ተፈቅዶአልን? ወይስ አልተፈቀደም? አሉት። |
አሁንም ይህች ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንደማይሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መንግሥትን ይጐዳል።
ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድለናል፤ ስለ ኀጢአታችን እኛና ልጆቻችን ንጉሦቻችን፥ ካህናቶቻችንም ለሰይፍና ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለዕፍረት በአሕዛብ ነገሥታት እጅ ተጣልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊታችን እፍረት እንኖራለን።
ስለ ኀጢአታችንም ለሾምህብን ነገሥታት በረከቷን ታበዛለች፤ ሰውነታችንንም ይገዛሉ፤ በእንስሶቻችንም የሚወድዱትን ያደርጋሉ፤ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን።
“አዎን ይገብራል” አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ሆይ! ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥና ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው? ወይስ ከእንግዶች?” አለው።
እነርሱም እንዲህ ብለው ጠየቁት፥ “መምህር ሆይ፥ አንተ እውነት እንደምትናገርና እንደምታስተምር፥ ፊት አይተህም እንደማታዳላ፥ የእግዚአብሔርንም መንገድ በቀጥታ እንደምታስተምር እናውቃለን።
እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄሣር ግብር እንዳይሰጡ ሲከለክልና ሕዝቡን ሲያሳምፅ፥ ራሱንም የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስን ሲያደርግ አገኘነው።”
ከእርሱም በኋላ ሰዎች ለግብር በተቈጠሩበት ወራት ገሊላዊው ይሁዳ ተነሣ፤ ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ እርሱም ሞተ፤ የተከተሉትም ሁሉ ተበታተኑ።
ለሁሉም እንደሚገባው አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ስጡ፤ ዐሥራት ለሚገባው ዐሥራትን ስጡ፤ ሊፈሩት የሚገባውን ፍሩ፤ ክብር የሚገባውንም አክብሩ።
ከወንድሞችህ መካከል አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን ለአንተ አለቃ ትሾማለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ሌላ ሰው በአንተ ላይ መሾም አትችልም።