ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
ሉቃስ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበኵር ልጅዋንም ወለደች፤ አውራ ጣቱንም አሰረችው፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በበረትም አስተኛችው፤ በማደርያቸው ቦታ አልነበራቸውምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበኩር ልጇንም ወለደች፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። |
ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
እንዲህም ሆነ፥ ወደምናድርበትም ስፍራ በደረስን ጊዜ ዓይበታችንን ከፈትን፤ እነሆም፥ የየአንዳንዱ ሰው ብር በየዓይበቱ አፍ ነበር፤ አሁንም ብራችንን በእጃችን እንደ ሚዛኑ መለስነው።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
ወደ እርሱም ቀረበ፤ ቍስሉንም አጋጥሞ አሰረለት፤ በቍስሉ ላይም ወይንና ዘይት ጨመረለት፤ በአህያውም ላይ አስቀምጦ እንዲፈውሰው የእንግዶችን ቤት ወደሚጠብቀው ወሰደው፤ የሚድንበትንም ዐሰበ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸርነቱን ታውቃላችሁ፤ በእርሱ ድህነት እናንተ ባለጸጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለጸጋ ሲሆን፥ ስለ እናንተ ራሱን ድሃ አደረገ።