ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቆላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ።
ሉቃስ 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘንድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚያች መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለ ነበርም፣ ሊያየው ወደ ፊት ሮጦ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም መንገድ ማለፍ ነበረበትና ወደ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ዘኬዎስ እርሱን ለማየት ብሎ ከሕዝቡ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። |
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቆላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ።
በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን፥ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባንም እንጨት በብዛት በቆላ እንደሚገኝ ሾላ በይሁዳ አኖረ።
ንጉሡም ወርቁንና ብሩን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባውንም እንጨት በቆላ እንደሚበቅል ሾላ ብዛት አደረገው።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ብትኖራችሁ ይህችን ሾላ ከሥርሽ ተነቅለሽ በባሕር ውስጥ ተተከዪ ብትሉአት ትታዘዝላችኋለች።”
ጌታችን ኢየሱስንም ያየው ዘንድ፥ ማን እንደ ሆነም ያውቅ ዘንድ ይሻ ነበር፤ የሰው ብዛትም ይከለክለው ነበር፤ ቁመቱ አጭር ነበርና።
ጌታችን ኢየሱስም ወደዚያ በደረሰ ጊዜ አሻቅቦ አየውና፥ “ዘኬዎስ ሆይ፥ ፈጥነህ ውረድ፤ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ አለኝና” አለው።
ሰውም ተጨናንቆ ነበርና የሚያስገቡበት አጡ፤ ወደ ሰገነትም ወጡ፤ ጣራውንም አፍርሰው ወደ ቤቱ ውስጥ በጌታችን በኢየሱስ ፊት ከነአልጋው አወረዱት።