ሉቃስ 19:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ላለው ሁሉ ይሰጡታል፤ ይጨምሩለታልም፤ የሌለውን ግን ያን ያለውንም ቢሆን ይወስዱበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም እንዲህ አለ፤ ‘እላችኋለሁ፤ ላለው ይጨመርለታል፤ የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል እላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌትዮውም ‘ላለው ሁሉ ይበልጥ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል እላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል። |
ያም መጋቢ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምን ላድርግ? አሁን ጌታዬ ከመጋቢነቴ ይሽረኛል፤ ማረስ አልችልም፤ ለመለመንም አፍራለሁ።
እንግዲህ እንዴት እንደምትሰሙ አስተውሉ፤ ላለው ይሰጠዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።”
በመዝሙር መጽሐፍ ‘መኖሪያዉ ምድረ በዳ ትሁን፤ በውስጧም የሚኖር አይኑር፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ’ ተብሎ ተጽፎአልና።
ሳሙኤልም፥ “እግዚአብሔር ከእስራኤል መንግሥትህን ዛሬ ከእጅህ ቀደዳት፤ ከአንተም ለሚሻል ለባልንጀራህ አሳልፎ ሰጣት፤
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።