ሉቃስ 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳዊውም ቆመና እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማኞችና እንደ ዐመፀኞች፥ እንደ አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ያላደረግኸኝ አመሰግንሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳዊውም ቆሞ ስለ ራሱ እንዲህ ይጸልይ ነበር፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ እንደ ሌላው ሰው ሁሉ ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ይልቁንም እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ባለመሆኔ አመሰግንሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፥ ቀማኛና ዐመፀኛ አመንዝራም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ |
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
ነገር ግን ጽድቅን እንደሚያደርግ የአምላኩንም ፍርድ እንደማይተው ሕዝብ ዕለት ዕለት ይሹኛል፤ መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ። አሁንም እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አትቅረቡ” ይላሉ። ስለዚህም የቍጣዬ ጢስ በዘመኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነድድባቸዋል።
ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ግን ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ፤ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ። በኢየሩሳሌምም በመንገዶችዋ ቍጥር ለጣዖት ሠዉ።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”
‘ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ፤ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም፤’ የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥