ሉቃስ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታውም ጠርቶ፦ ‘በአንተ ላይ የምሰማው ይህ ነገር ምንድን ነው? እንግዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አስጠራውና፣ ‘ይህ የምሰማብህ ምንድን ነው? ከእንግዲህ አንተ መጋቢ ልትሆነኝ ስለማትችል፣ የምታስተዳድረውን ንብረት መቈጣጠሪያ ሒሳብ አስረክበኝ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠርቶም ‘ይህ የምሰማብህ ነገር ምንድነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ፤’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታሙም ሰው መጋቢውን አስጠርቶ ‘ይህ የምሰማብህ ነገር ምንድን ነው? ከእንግዲህ ወዲህ መጋቢዬ ልትሆን አትችልምና በመጋቢነትህ የሠራህበትን የንብረቴን ሒሳብ አቅርብልኝ’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠርቶም፦ ይህ የምሰማብህ ምንድር ነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ አለው። |
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተሰቡ ላይ የሚሾመው ደግ ታማኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?
ጌታችን ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ገንዘቡን ሁሉ እንደሚበትን አድርገው በእርሱ ዘንድ ከሰሱት።
ያም መጋቢ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምን ላድርግ? አሁን ጌታዬ ከመጋቢነቴ ይሽረኛል፤ ማረስ አልችልም፤ ለመለመንም አፍራለሁ።
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
መልካም ቢሆን፥ ክፉም ቢሆን በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን እንቀበል ዘንድ፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለንና።
ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤
ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።