La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ይህ ልጅህ ንብረትህን ከጋለሞቶች ጋራ አውድሞ ሲመጣ፣ የሠባውን ፍሪዳ ዐረድህለት።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፍሪዳ አረድህለት፤’ አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህ ልጅህ ግን ሀብትህን ከአመንዝራ ሴቶች ጋር አባክኖ በተመለሰ ጊዜ የሰባውን ወይፈን ዐረድክለት።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ገንዘብህን ከጋለሞቶች ጋር በልቶ ይህ ልጅህ በመጣ ጊዜ፥ የሰባውን ፊሪዳ አረድህለት አለው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 15:30
10 Referencias Cruzadas  

ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በጽኑ እጅ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኸው በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለምን ተቈ​ጣህ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኻ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና ሂድ፤ ፈጥ​ነህ ውረድ።


ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፤” አላቸው።


መል​ሶም አባ​ቱን እን​ዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ፈጽሞ ከት​እ​ዛ​ዝህ አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ለእኔ ግን ከባ​ል​ን​ጀ​ሮች ጋር ደስ እን​ዲ​ለኝ አንድ የፍ​የል ጠቦት እንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም።


አባ​ቱም እን​ዲህ አለው፦ ‘ልጄ አን​ተማ እኮ ዘወ​ትር ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው።


ነገር ግን ይህ ወን​ድ​ምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖ​አ​ልና፥ ጠፍ​ቶም ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤ​ትም ልና​ደ​ርግ ይገ​ባል።”


ፈሪ​ሳ​ዊ​ውም ቆመና እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፦ ‘አቤቱ እንደ ሌሎች ሰዎች፥ እንደ ቀማ​ኞ​ችና እንደ ዐመ​ፀ​ኞች፥ እንደ አመ​ን​ዝ​ሮ​ችም፥ ወይም እን​ደ​ዚህ ቀራጭ ያላ​ደ​ረ​ግ​ኸኝ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።