ሉቃስ 12:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ያ ክፉ አገልጋይ በልቡ፦ ጌታዬ ቶሎ አይመጣም ቢል፥ በጌታው ቤት ያሉትንም ወንዶችንና ሴቶችን አገልጋዮች ሊደበድብና ሊያጕላላ ቢጀምር፥ ከሰካራሞችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥ ቢሰክርም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ያ ባሪያ፣ ‘ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፤ ይዘገያል’ ብሎ ቢያስብና ወንድና ሴት ብላቴኖችን ቢደበድብ፣ ደግሞም እንዳሻው ቢበላና ቢጠጣ መስከር ቢጀምር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያ ባርያ ግን ‘ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል’ ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም ይሰክርም ዘንድ ቢጀምር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ያ አገልጋይ ‘ጌታዬ ቶሎ አይመጣም፤ ይዘገያል’ ብሎ በማሰብ እየበላ፥ እየጠጣ፥ እየሰከረም ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን መምታት ይጀምራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ ባሪያ ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም ይሰክርም ዘንድ ቢጀምር፥ |
እነሆ፥ በፊቴ ተጽፎአል፦ ኀጢአቶቻችሁንና የአባቶቻችሁን ኀጢአት በአንድ ላይ ወደ ብብታቸው ፍዳ አድርጌ እመልሳለሁ እንጂ ዝም አልልም፤ ይላል እግዚአብሔር፤
ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን ገረፈው፤ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው አዘቅት ውስጥ ጣለው።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኞች ስለሌሉ፥ እረኞችም በጎችን ስላልፈለጉ፥ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎችን ስላላሰማሩ፥ በጎች ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎችም ለዱር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና፤
የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠረጠረው ዕለት፥ ባላወቀውም ሰዓት መጥቶ ከሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርገዋል።
“ራሳችሁን ጠብቁ፤ በመብልና በመጠጥ፥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ፤ ያቺ ቀንም በድንገት ትደርስባችኋለች።
አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መልካሙን የወይን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል፤ ከጠገቡ በኋላም ተርታውን ያመጣል፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን አቈየህ” አለው።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤
የሚገዙአችሁንና የሚቀሙአችሁን፥ መባያ የሚያደርጓችሁንና የሚታበዩባችሁን፥ ፊታችሁንም በጥፊ የሚመትዋችሁን ትታገሡአቸዋላችሁና።
እናንተም፥ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁም፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ ውስጥ የተቀመጠው ሌዋዊም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
የዐመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤