ሉቃስ 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እህሌን የማኖርበት የለኝምና ምን ላድርግ ብሎ በልቡ ዐሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሰው፣ ‘ምርቴን የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ አሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም በሐሳቡ፥ ‘ይህን ሁሉ እህል የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ?’ እያለ ያሰላስል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ። |
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
ከዚህ በኋላ አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈትነው ተነሣና፥ “መምህር ሆይ፥ የዘለዓለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” አለው።
እርሱም አለ፦ እንዲህ አደርጋለሁ፤ የቀድሞውን ጎተራዬን አፈርሳለሁ፤ ከእርሱ የሚበልጥ ሌላ ጎተራም እሠራለሁ፤ እህሌንና በረከቴንም በዚያ እሰበስባለሁ።
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።
ሀብታችሁን ሸጣችሁ ምጽዋት ስጡ፤ ሌባ በማያገኝበት ነቀዝም በማያበላሽበት፥ የማያረጅ ከረጢት፥ የማያልቅም መዝገብ በሰማያት ለእናንተ አድርጉ።
ያም መጋቢ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምን ላድርግ? አሁን ጌታዬ ከመጋቢነቴ ይሽረኛል፤ ማረስ አልችልም፤ ለመለመንም አፍራለሁ።
እኔም እላችኋለሁ፦ ባለቀባችሁ ጊዜ እነርሱ በዘለዓለም ቤታቸው ይቀበሉአችሁ ዘንድ በዐመፃ ገንዘብ ለእናንተ ወዳጆች አድርጉበት።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ሰምቶ እንዲህ አለው፥ “አንዲት ቀርታሃለች፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለነዳያን ስጥ፤ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ።”
ጌታውም፦ መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለሆንህ በብዙ ላይ እሾምሃለሁ፤ በዐሥሩ ከተሞች ላይ ተሾም አለው።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።