Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 16:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ወደ ውጭም አው​ጥቶ “ጌቶች፥ እድን ዘንድ ምን ላድ​ርግ?” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ይዟቸው ከወጣ በኋላ፣ “ጌቶች ሆይ፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ወደ ውጭም አውጥቶ “ጌቶች ሆይ! እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ወደ ውጪም አወጣቸውና “ጌቶቼ ሆይ! ለመዳን ምን ማድረግ ይገባኛል?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ወደ ውጭም አውጥቶ፦ “ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 16:30
16 Referencias Cruzadas  

ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ልባ​ቸው ተከ​ፈተ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ወን​ድ​ሞቹ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ምን እና​ድ​ርግ?” አሏ​ቸው።


‘አቤቱ፥ ጌታዬ ምን ላድ​ርግ?’ አልሁ፤ ጌታም፦ ‘ተነ​ሥና ወደ ደማ​ስቆ ሂድ፤ ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህ​ንም ሁሉ በዚያ ይነ​ግ​ሩ​ሃል’ አለኝ።


እን​ዲ​ህም አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እኛስ እንደ እና​ንተ የም​ን​ሞት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታ​ችሁ ሰማ​ይና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ያለ​ውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ለሱ ዘንድ ወን​ጌ​ልን እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን።


ሕዝ​ቡም፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ርግ?” ብለው ጠየ​ቁት።


እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤


ያን ጊዜ ትጠ​ራ​ለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ማ​ሃል፤ ትጮ​ኻ​ለህ፤ እር​ሱም፦ እነ​ሆኝ፥ ይል​ሃል። የዐ​መፅ እስ​ራ​ትን ከመ​ካ​ከ​ልህ ብታ​ርቅ፥ ጣት​ህ​ንም መጥ​ቀስ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ር​ንም ብት​ተው፥


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


እር​ሱም ትእ​ዛ​ዙን ተቀ​ብሎ ወደ ውስ​ጠ​ኛው ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም በግ​ንድ አጣ​ብቆ ጠረ​ቃ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ጳው​ሎ​ስ​ንና እኛን እየ​ተ​ከ​ተ​ለች፥ “እነ​ዚህ ሰዎች የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ የሕ​ይ​ወ​ት​ንም መን​ገድ ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ች​ኋል” እያ​ለች ትጮኽ ነበር።


እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው።


ጻድቅ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ንጹሕ ይሆ​ናል? ከሴ​ትስ የተ​ወ​ለደ ራሱን ንጹሕ ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?


የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ይማራሉና።


ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው።


እኔ ራሴ አያ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ሐሰ​ት​ንም ተና​ግሬ እንደ ሆነ፥ ደግሜ እን​ዳ​ል​ሠራ አንተ አሳ​የኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios