አባቶቻቸው ከግብፅ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፤ በቀንና በሌሊት ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባቸው ነበር፤ አዎ ልኬባቸዋለሁ።
ሉቃስ 11:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ፤ እነርሱ አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ ሌሎችንም ያሳድዳሉ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ “ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ትላለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ አንዳንዶችን ይገድላሉ፤ የቀሩትንም ያሳድዳሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ ወደ እርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል፥ |
አባቶቻቸው ከግብፅ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፤ በቀንና በሌሊት ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባቸው ነበር፤ አዎ ልኬባቸዋለሁ።
የአባቶቻችሁም ሥራ ደስ አሰኝቶአችኋል፤ የምትመሰክሩባቸውም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እነርሱ የገደሉአቸውን መቃብራቸውን እናንተ ትሠራላችሁና።
ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፥ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮች ትሆኑኛላችሁ።”
ሳውል ግን ገና አብያተ ክርስቲያናትን ይቃወም ነበር፤ የሰውንም ቤት ሁሉ ይበረብር ነበር፤ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።
ለእኛ ለዳንነው ግን ከአይሁድ፥ ከአረሚም ብንሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።
እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦቹም ሐዋርያትን፥ ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን፥ ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ።